የአገልግሎት ውልና መመሪያ (Terms & Conditions)
እንኳን ወደ አዲስ ቤት ኪራይ (Addis Bet Kiray) በደህና መጡ። ይህንን ድረ-ገጽ ሲጠቀሙ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የአገልግሎት ህጎችና መመሪያዎች ማንበብዎን እና መስማማትዎን ያረጋግጣሉ።
1. የመድረኩ ሚና እና ኃላፊነት
- አዲስ ቤት ኪራይ (Addis Bet Kiray) አከራዮችን እና ተከራዮችን ያለ ደላላ በቀጥታ የሚያገናኝ መድረክ (Online Listing Platform) ብቻ ነው።
- መድረኩ የቤቶቹ ባለቤት ወይም አከራይ አይደለም፤ እንዲሁም በአከራይና በተከራይ መካከል ለሚደረግ የኪራይ ውል ወይም የገንዘብ ልውውጥ ኃላፊነት አይወስድም።
2. የአከራዮች ግዴታ እና የማስታወቂያ ህጎች
- አከራዮች የሚለጥፉት የቤት መረጃ፣ ፎቶ እና ዋጋ እውነተኛ እና ትክክለኛ መሆን አለበት።
- ያለ ባለቤት ፈቃድ የሌላ ሰውን ቤት ወይም የተሳሳተ የስልክ ቁጥር ማስገባት በህግ ያስጠይቃል፤ መለያዎም (Account) ያለ ማስጠንቀቂያ ይታገዳል።
- ቤቱ እንደተከራየ አከራዩ ወዲያውኑ ወደ «የእኔ ቤቶች» በመግባት ማስታወቂያውን «ተከራይቷል» በሚል ሁኔታ ማስተካከል ወይም ማጥፋት አለበት።
3. የአገልግሎት ክፍያ (Listing Fee)
- አንድ ቤት በዋናው ገጽ ላይ ታይቶ ለተከራይ እንዲተዋወቅ የአገልግሎት ክፍያ በቤቱ የወር ኪራይ መጠን ላይ ተመስርቶ ይከፈላል፦ ለመደበኛ (Standard) ማስታወቂያ 3%፣ ለልዩ (VIP) ማስታወቂያ ደግሞ 5% በራሱ ተሰልቶ ይከፈላል።
- የተሰላውን ትክክለኛ ክፍያ በቴሌብር ወይም በባንክ በማስገባት የግብይት መለያ ቁጥር (Transaction ID) ማስገባት አለብዎት።
- የሀሰት የክፍያ ደረሰኝ ቁጥር ማስገባት መለያዎን ለዘለቄታው ያሳግዳል።
- አንዴ የተከፈለ እና የጸደቀ የማስታወቂያ ክፍያ ተመላሽ (Refund) አይደረግም።
4. ለተከራዮች የሚሰጥ ጥንቃቄ
- ተከራዮች ቤቱን በአካል ሳያዩ፣ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሳያረጋግጡ እና ህጋዊ የኪራይ ውል ሳይፈራረሙ ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ (እጅ መያዣ) ለማንም ሰው እንዳይከፍሉ በጥብቅ እናሳስባለን።
ማሳሰቢያ፦ አስተዳደሩ (Admin) በማንኛውም የሚለጠፍ ማስታወቂያ ላይ የማጣራት፣ የማስተካከል ወይም የማጥፋት መብቱ የተጠበቀ ነው።